Skip to content Skip to footer

ዘውትር በመንፈስ ለመጸለይ እንተጋለን (ኤፌ 6:18፤ ይሁዳ 20)፤ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትን ፈልገን፣ መንፈሱን፣ ምህረቱን፣ ጸጋውን፣ የጸጋ ስጦታዎቹንም ለመቀበል በህብረት ወደ ፊቱ እንቀርባለን (ሉቃ 11:13፤ ዕብ 4:16፤ 1 ቆሮ 1:9፤ 12-14)፤ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናውም ስለሰዎች ሁሉ ስለመሪዎች፣ ስለአስተዳዳሪዎች እናደርጋለን (1 ጢሞ 2:2)፣ ሰው ሁሉ እንዲድን እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ እንጸልያለን (2 ጢሞ 2:4)፣ ለመበዝበዝ አስቀድመን ኃይለኛውን እናስራለን (ማቴ 12:29፤ ማር 3:27)፤ በጸሎት በምልጃ በምስጋና ልመናችንን እናስታውቃለን (ፊል 4:6)፤ የሕይወት ትግል ላለባቸው (የኑሮ ውጣ ውረድ፣ የመንፈሳዊ ሕይውት ትግል፣ ሕመምና ደዌ ላለባቸው) እንጸልያለን (ፊል 4:6፣ ያዕ 5:14)፤ ስምቶ እንደሚቀበለን፣ እንደሚረዳን፣ ፊቱን እንደሚመልስልን፣ እጁን እንደሚዘረጋልን፣ የሚሳነው ነገር እንደሌለ እናምናለን (ኤር 33:1-3፤ ኤር 32:26-27 ማቴ 7:7፤ ሉቃ 18፤1-8፤ 1 ዮሐ 5:14)

  • ከሰኞ እስከ ዓርብ ከምሽቱ 7 በሚጀምሩ ፕሮግራሞች በስልክ ቁጥር 339-209-4169 ገብተውአብረውንይጸልዩ
  • የግልየጽሎትርዕስካልዎትበሚከተለውመንገድያግኙን፦
  • በስልክ፦ +1 972-762-8079 
  • በኢሜል info@eecii.org